የጂቡቲ የቢዝነስ ልዑክ በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ቦታዎችን ጎበኘ

የኦስትሪያ እና የጁቡቲ ኩባንያዎች በመጣመር በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማየት የተለያዩ የኢንዱስትሪ ስፍራዎችን ጎብኝቷል።

የቢዝነስ ልዑኩ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

ልዑኩ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ስፍራዎችን መጎብኘቱን በጁቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የቢዝነስ ልዑኩ ባለፈው ሳምንት በኤምባሲው ተገኝቶ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች በተመለከተ በጁቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ጋር በስፋት መወያየታቸውም ተጠቅሷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *