የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን የአሰራርና የቁጥጥር ስርዓር ማዘመን እንደሚገባ ተጠቆመ

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስርዓትን በጋራ ማሳለጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ዜጎች ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት እንዲያገኙና መብትና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተጀምሩ ሥራዎችን ተመልክተዋል።

በዘርፉ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ ዜጎች መብትና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ሁሉም አስፈፃሚ አካላት በጋራ እየሰሩ ያሉትን ተግባራት በማጠናከር የአሰራርና የቁጥጥር ስርዓቱን ማዘመን  እንደሚገባ ተጠቅሷል።

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የምልመላ ሂደቱን ለማሳለጥ፣ግልጸኝነትን ለማጎልበት እና በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎችን ደህንነት በማረጋገጥ ከብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት ለመስጠት ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሂደት በየደረጃው ያሉ አመራሮች ወሳኝ ሚና እንዳላቸውም ተገልጿል።

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በኢትዮ ቴሌኮም መካከል የተጀመረውን የቅንጅት ሥራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ መገለጹንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ተቋማቱ ካለፈው ልምድ በመውሰድ የዜጎችን መብትና ደህንነት እንዲሁም ተጠቃሚነት በአግባቡ እንዲረጋገጥ በትኩረት ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነትም ገልፀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *