የኢትዮጵ አየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ አገልግሎት ጀመረ።

በዚህም አየር መንገዱ በአፍሪካ ያሉትን የጭነት መዳረሻዎች ብዛት ወደ 35 አሳድጓል።

አዲሱን በረራ አስመልክቶ የኢትዮጵ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ አገልግሎት መስጠት በመጀመራችን ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል የኢትዮጵ አየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው።

ይህ በረራ የሰሜን አፍሪካን የመግሪብ ቀጠና ወደ ዓለም-አቀፉ የጭነት አገልግሎት መዳረሻዎቻችን ያካተተ በመሆኑ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሆኗል ብለዋል።

የዚህ በረራ መጀመር በአፍሪካ ያለንን የዕቃ ጭነት መዳረሻ ቁጥር 35 ሲያደርስ፤ በተመሳሳይ ብሔራዊ አየር መንገዱ በእቃ ጭነት አገልግሎት ዘርፍ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭነት በረራ መዳረሻዎች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ እና በዓለም የአየር የዕቃ ጭነት አገልግሎት መስክ ቁልፍ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ የዓለም ንግድ እና ሸቀጦች ፍሰትን ለማሳለጥ አዳዲስ የጭነት መስመሮችን በመክፈት አገልግሎቱን በዓለም ዙሪያ ማስፋፋቱን ይቀጥላል ብለዋል።

ወደ ካዛብላንካ የምናደርገው የጭነት በረራ በዘመናዊው እና ከ100 ቶን በላይ የመሸከም አቅም ባለው ቦይንግ 777-200F የእቃ ጭነት አውሮፕላን የሚደረግ መሆኑን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።”

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *