የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሶስት የቻይና ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሶስት የቻይና ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ከኩባንያዎቹ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተፈራርመውታል።

ስምምነቱ ከሁለት ፋርማሲዩቲካል እና አንድ በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ ከተሰማራ ኩባንያ ጋር የተፈረመ መሆኑን ኮሚሽነሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በስምምነቱ መሰረት ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚሰማሩ ሲሆን፣ ይህም ለኢኮኖሚው ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ኮሚሽነሯ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *