የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባንጉይ በረራ ጀመረ

የኢትጵያ አየር መንገድ ወደ ሴንትራል አፍሪካ ዋና ከተማ ባንጉይ በረራ ጀምሯል።

የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያዴቻ÷ በ2030 ወደ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ዋና ከተሞች የመብረር እቅድ መኖሩን አንስተዋል።

አየር መንገዱ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የበረራ መዳረሻዎችን እያሰፋና የአውሮፕላን ቁጥሮችንም እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለትም ወደ ሴንትራል አፍሪካ ባንጉይ የጀመረው በረራ በአፍሪካ የበረራ መዳረሻዎቹን ወደ 64 አድርሶታል ነው ያሉት።

አየር መንገዱ በሳምንት ሶስት ጊዜ ወደ ባንጉይ በረራ እንደሚያደርግም አመላክተዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *