የቻይና የኢንቨስትመንት ልዑክ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኘ

 ከቻይና ጂሊን ግዛት እና ፉያንግ አስተዳደርና ከተለያዩ አምራች ኩባንያዎች የተውጣጣ የልዑካን ቡድን የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝቷል።

ልዑኩ የጂሊን ግዛት የቋሚ ኮሚቴ ምክትል ጸሀፊ ፋንን ጨምሮ የፉያንግ አስተዳደር ምክትል ሴክሬታሪ ጄኔራል ዋንግ ፈሂሁ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቻይና የወዳጅነት እና ትብብር ኮሚቴ ሊቀመንበር ቤቲ ዙ የተመራ ነው ተብሏል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀጋዬ ዘካሪያስ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎችን እንቅስቃሴ ለልዑኩ ማስጎብኘታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።

በዚህም ኮርፖሬሽኑ ያዘጋጃቸውን የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም ማበረታቻዎችን ጨምሮ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም በቀጣይ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል ተብሏል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *