የቻይናው ዘኒት ስቲል ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት አለኝ አለ

 በቻይና ብረታብረቶችንና የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን አምራቹ ዘኒት ስቲል ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከኩባንያው የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በርካታ ቻይናውያን ባለሃብቶች መኖራቸውን ተከትሎ ኮርፖሬሽኑ የቻይና ኢንቨስትመንት ዴስክ ከፍቶ እየሰራ መሆኑን አቶ አክሊሉ አስረድተዋል።

የኩባንያው ኃላፊዎችም÷ ስለ ኢንቨስትመንት ዕቅዱ እንዲሁም ኩባንያው ያለበትን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ እና በመጀመሪያ ምዕራፍ ሊያከናውኗቸው ያሰቧቸውን ስራዎች አብራርተዋል።

ኩባንያው ወደ ስራ ሲገባም በመጀመሪያው ምዕራፍ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ 30 ሄክታር የለማ መሬት በመረከብ ከ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስት የማድረግ ዕቅድ እንዳላው ጠቁመዋል።

በቀጣይም በሌሎች ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና ከ100 ሄክታር በላይ የለማ መሬት በመረከብ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *