የተከበሩ አቶ አህመድ ሺዴ በቤጂንግ የሚገኘውን የአሊባባ ቡድን ዋና መሥሪያ ቤትን ጎበኙ

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን መሪ የኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ በቤጂንግ የሚገኘውን የአሊባባን ቡድን ዋና መሥሪያ ቤት ጎብኝተዋል። በዕለቱ ከአሊባባ ቡድን ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር ሊዩ ናን ጋር ተወያይተዋል።

የልዑካን ቡድኑ በአሊባባ ታሪክ፣ ልማት እና የወደፊት ትንበያ ላይ በኤግዚቢሽኑ አዳራሽ ተገኝቶ ከአሊባባ አመራሮች ጋር በኢትዮጵያ እና በቡድኑ ኢ-ኮሜርስ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ የወደፊት ትብብር ላይ ውጤታማ ውይይት አድርጓል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *