የሳይመንስ ኩባንያ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ልማት አማራጮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

 የሳይመንስ ኢነርጂ ኩባንያ በኢትዮጵያ ባሉት የኢነርጂ ልማት አማራጮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ተገለፀ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር፣ ኢ/ር) በኢትዮጵያና በአፍሪካ ህብረት የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አወር እና ከሳይመንስ ኢነርጂ ኩባንያ ተወካይ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በኢነርጂ ልማት ኢንቨስትመንት ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን በዚህ ወቅት ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር፣ ኢ/ር)÷ የሀይል አቅርቦት ብቃትና ውጤታማነት ላይ የሚያግዙ የግሉ ዘርፍ ኩባንያዎች በታዳሽ ሀይል ልማት ዘርፍ እንዲሰማሩ ፍላጎት መኖሩን አንስተዋል።

ከውሃ፣ ከነፋስ፣ ከጸሀይ ሀይልና ከጅኦተርማል ሀይል ለማመንጨት የተለዩ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም መጥቀሳቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

አምባሳደር ስቴፍን አወር በበኩላቸው÷ በኢነርጂ ልማት ዘርፍ ትልቅ ከሆኑት ድርጅቶች መካከል የሆነው የሳይመንስ ኢነርጂ ኩባንያ በኢትዮጵያ ባሉት የኢነርጂ ልማት አማራጮች ላይ ለመሳተፍ ያለውን ፍላጎት ተናግረዋል።

የሳይመነስ ኢነርጂ ኩባንያ የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ፈራንሲዮስ ዣቪየር ዱቢየስ ÷ኩባንያው በዓለም ግዙፍ ከሚባሉት የኢነርጂ ኩባንያዎች መካከል መሆኑን ገልፀው በአንዳንድ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትም ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ መሆኑን አንስተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *