የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስያና መካከለኛው ምስራቅ በሚላክ የቡና ምርት ላይ በማጓጓዣ ክፍያ በአንድ ኪሎ ግራም እስከ 1 ነጥብ 50 ዶላር ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።
የአየር መንገዱ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቡና ላኪዎችን ለማበረታታት እና የኢትዮጵያን ቡና በዓለም ለማስተዋወቅ የሚጫወተውን ሚና ማጠናከሩን ገልጿል።
በዚህም ወደ እስያ እና መካከለኛው ምስራቅ በሚልኩት የቡና ምርት ላይ በአንድ ኪሎ ግራም እስከ 1 ነጥብ 50 ዶላር ድረስ ቅናሽ ማድረጉን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ