አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክሲዮን ማህበር ከሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን አክሲዮን ማህበር ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።
የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዳንኤል በቀለ ÷ደንበኞች አማራጭና ቀላል የክፍያ አማራጮችን በአነስተኛ የገንዘብ ልውውጥ ክፍያ መጠቀም እንዲችሉ ከሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ አክሲዮን ማህበር ጋር ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል።
አክሲዮን ማህበሩ ከ27 ማርኬቲንግና ብራንዲንግ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት መፈራረሙንም አስታውቀዋል።
አሸዋ ቴክኖሎጂ ከ15 በላይ ሶፍትዌሮችን አበልጽጎ ለተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ማቅረቡም ተመላክቷል።
አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክሲዮን ማህበር ከ325 ሚሊየን ብር በላይ ጠቅላላ ካፒታል ማስመዝገቡም የተገለጸ ሲሆን÷ እስካሁን ለ200 ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩም ተጠቁሟል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ