ቻይና በዓመቱ ከፍተኛ መኪና አቅራቢ ሀገር መሆኗ ተገለፀ

ቻይና በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2023 አውቶሞቢሎችን ወደ ወጭ ገቢያ በማቅረብ ቀዳሚ ሀገር መሆኗን ተገለፀ።

የኤሲያው ፋይናንሺያል ጋዜጣ እንዳስታወቀው÷ ሀገሪቱ እስከ አመቱ መጨረሻ 4 ነጥብ 41 ሚሊዮን አውቶሞቢሎችን ወደ ውጭ ገብያ የላከች ሲሆን ይህም በ2022 ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር 58 በመቶ ከፍ ብሏል።

በዚህም ቻይና 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን መኪኖችን ለውጭ ገቢያ ያቀረበችውን ጃፓን በመብለጥ በመኪና  ሽያጭ ቀዳሚውን ስፍራ መያዝ ችላለች።

ቻይናበቀጣይም በኤክትሪከ መኪኖች ምርት ላይ ትኩረቷን በማድረግ በአለም የመኪና ገብያ ውስጥ ቀዳሚነቷን ለማስጠበቅ እንደምትስራ መግለጿ ተመላክቷል።

ቻይና በመኪና ሽያጭ ቀዳሚ መሆን የቻለችው በሩሲያ በተጣለው ማዕቀብ ምክንያት የጃፓን እና ምዕራባውያን መኪኖች በሩሲያ ገብያ ባለመቅረባቸው መሆኑ ነው የተገለፀው።

እንደ መፅሄቱ መረጃ ከባለፈው ዓመት ጥር ወር ጀምሮ እስከ ጥቅምት ባሉት ጊዜያት ቻይና 730 ሺህ ዩኒት ተሸከርካሪዎችን ለሩሲያ ሸጣለች።

ሜክሲኮ ሁለተኛዋ የቻይና መኪና ሽያጭ መዳረሻ ሀገር ስትሆን እስከ አመቱ መጨረሻ ቻይና 330 ሺህ ዩኒት በላይ መኪኖችን ለሜክሲኮ መሸጧን አር ቲ ዘግቧል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *