ባለፉት አራት አመታት የወጪ ንግድ ዘርፉ በአማካይ ሰባት በመቶ እድገት አሳይቷል ተባለ

በኢትዮጵያ ባለፉት አራት አመታት የወጪ ንግድ ዘርፉ ላይ በትኩረት በመሰራቱ በአማካኝ ሰባት በመቶ ዉጤት ማስመዝገብ ተችሏል ሲል የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከውጭ ንግድ ዘርፎች ውስጥ የግብርና ዘርፍ ከፍተኛ ድርሻ ነበረዉ፡፡ ከግብርናው ዘርፍ በዋነኝነት ቡና የቅባት እህሎችና አበባ እንዲሁም ጫት ይጠቀሳሉ፡፡ የቡና እና አበባ ምርቶች ከታቀደው በላይ ትርፍ የታየባቸው ዘርፎች ናቸው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የማዕድን ዘርፍ ጥሩ የሚባል እድገት እያሳየ ያለ ዘርፍ ሲሆን ወርቅ ወደ ውጭ በማቅረብ ዉጤት እየተመዘገበ ይገኛል፡፡
በመቀጠልም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች በሶስተኛ ደረጃ ለውጪ ገበያ እየቀረቡ ነዉ፡፡

ከእነዚህም በተጨማሪ ባለፉት 4 አመታት የአገልግሎት ወጪ ንግድ ላይ እድገት ታይቷል፡፡

በአገልግሎት ዘርፍ በ2012 ዓ.ም 4.69 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ሲሆን 4.7 ቢሊየን ዶላር አፈፃፀም ተመዝግቧል ነው የተባለው፡፡

በዕቅዱ ማብቂያ አመት በ2015 በጀት አመት 6.07% የታቀደ ሲሆን በአፈጻጸሙ 7.1% መገኘት ተችሏል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *