በዱባይ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ለማስተዋወቅ ያለመ የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

በዱባይ እየተካሄደ ካለው 28ኛው ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም ለማስተዋወቅ ያለመ የቢዝነስ ፎረም ተካሄዷል፡፡

በዚህ ፎረም ላይ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የሚገኙና በኢትዮጵያ የመሰማራት አቅም ያላቸው ከ30 በላይ ኩባንያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እያስመዘገበች ስላለው ስኬት፣ በዘርፉ የግል ባለሀብቶች ሚና እና በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ነመራ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መልዕክተ ሳህሉ እና አምባሳደር አክሊሉ ከበደ በተዘጋጁ ሁለት የፓናል ውይይቶች ላይ በጉዳዩ ላይ ለተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዕድሎች በመጠቀም ውጤታማ የሆኑ የቢዝነስ ድርጅቶች ጋር ሁለተኛ ክፍል የፓናል ውይይት መካሄዱን በዱባይ እና ሰሜን ኢሚሬቶች የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

በውይይቱ በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎችን በመጠቀም ገብቶ መሥራት የሚያስገኛቸውን ጠቀሜታዎች ተወያዮቹ ለታዳሚው አስረድተዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *