በኢትዮጵያ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች በአንድ ወር ውስጥ ሰነድ ሊይዙ እንደሚገባ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ተቋሙ ቀርበው ሕጋዊ ሰነድ እንዲይዙ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሳስቧል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባደረገው ማጣራት በኢትዮጵያ ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው የሚኖሩ ፣ ሐሰተኛ ቋሚና ጊዜያዊ መኖሪያ ፈቃድ፣ ሐሰተኛ ፓስፖርትና ቪዛ እንዲሁም መኖሪያ ፈቃድ ሳያሳድሱ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች መኖራቸውን ገልጿል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ተቋሙ በሰራው የማጣራት ስራ ከ18 ሺህ በላይ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ዜጎች መገኘታቸው ተጠቁሟል።

በመሆኑም በኢትዮጵያ ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው
የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ከጥር 1 እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ባለው 1 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ እንዲመዘገቡ እና ወደ ህጋዊ የምዝገባ ስርአት እንዲገቡ ተቋሙ አሳስቧል።

ምንጭ፦ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *