ሳፋሪኮም በግማሽ ዓመት 34 ነጥብ 2 ቢሊየን የኬኒያ ሽልንግ የተጣራ ትርፍ አገኘ

ሳፋሪኮም በግማሽ ዓመት 34 ነጥብ 2 ቢሊየን የኬኒያ ሽልንግ የተጣራ ትርፍ ማኝኘቱን አስታወቀ።

የኬንያው ኩባንያ ጠንካራ ሆኖ እንደቀጠለ የገለጸ ሲሆን፥ በግማሽ ዓመቱ የ10 ነጥብ 9 በመቶ የገቢ እድገት በማስመዝገብ በአጠቃላይ 41 ነጥብ 6 ቢሊየን የኬኒያ ሽልንግ ገቢ ማግኘት መቻሉን አስታውቋል።

የአገልግሎት ገቢው 9 ነጥብ 3 በመቶ ያደገ ሲሆን፥ ይህም ወደ 158 ነጥብ 3 ቢሊየን የኬኒያ ሽልንግ አድጓል ማለት እንደሆነ ገልጾ፥ ይህም በዋነኛነት ኤም-ፔሳ እና ሌሎች አገልግሎቶች ተጠቃሽ እንደሆኑም ነው የተነሳው።

የገቢው እድገት ከኩባንያው ኤም-ፔሳ የፋይናንስ አገልግሎት ንግድ በተገኘ ገቢ ነው የተባለ ሲሆን፥ የኢንተርኔት ግንኙነት አቅርቦት ንግዱ እድገት ማሳየቱን የኬንያው ኔሽን ዘግቧል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *